ካብ ሰነ 1/2017 ዓ.ም ጀሚሩ ብምክትል ፕሬዜዳንት መዓርግ ኣማኻሪ ጉዳያት ፓለቲካ ፕሬዜዳንት ጊ/ም/ት ኮይኖም ተሸይሞም።

ሹመቱ በምርጫ ቦርድ የተሻረው ህወሓት በጊዚያዊ አስተዳደሩ ካቢኔ ያለውን ቦታ እጅግ ከፍ አድርጎታል።በጊዚያዊ አስተዳደሩ ካቢኔ ያለው የተፎኳኳሪ ፓርቲዎች ቦታ ከ3 አይበልጥም።ከሰኔ 1/2017 ዓ.ም ጀምሮ በትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት ታደሰ ወረደ (ሌ/ጀነራል) በምክትል ፕሬዜዳንት መአርግ የፓለቲካዊ ጉዳዮች አማካሪ ተደርገው የተሾሙት ኣለም  ገ/ዋህድ ፥ ከጦርነቱ በፊት እስከ አምና 2016 ዓ.ም ነሀሴ ተካሂዶ ህገ-ወጥ ነው የተባለው የህወሓት ጉባኤ ድረስ የድርጅቱ የፓለቲካዊ ጉዳዮች ሃላፊ በመሆን ሰርተዋል።በተጨማሪ ከጦርነቱ በፊትና በኋላ ከ5ቱ የህወሓት የፓሊት ቢሮ አባላት አንዱ በመሆን ሰርተዋል።በተካሄደው ጉባኤ ደግሞ ከነበሩበት የሃላፊነት ቦታ ወርደው የህወሓት የማእከላይ ኮሚቴ አባል እንዲሆኑ ‘የተገፉ’ ናቸው ተብሎ ሲነገርባቸው ቆይተዋል።ከያዝነው ወር ጀምሮ ደግሞ በጊዚያዊ አስተዳደሩ የከፍተኛ የሃላፊነት ቦታ ማግኘታቸውን ተከትሎ የደብረፅዮን (ዶ/ር) ህወሓት በሌ/ጀነራል ታደሰ ወረደ በሚመራው ካቢኔ ከፍተኛ ቁጥር የያዘ እንዲሆን አስችሎታል።

EthioNews #Ethiopia