
ዩኒቨርሲቲው ከመጀመሪያ እስከ ሦስተኛ ዲግሪ ፕሮግራሞች ያስተማራቸውን ከ6,800 በላይ ተማሪዎች አስመርቋል፡፡ ከተመራቂዎቹ መካከል 304 ምሩቃን በሦስተኛ ዲግሪ (PhD) ፕሮግራም ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቀቁ ናቸው፡፡ 352 በስፔሻሊቲ እና ሰብ-ስፔሻሊቲ ፕሮግራሞች እንዲሁም 2,859 በሁለተኛ ዲግሪ ፕሮግራም የተመረ ሲሆን፤ ቀሪዎቹ 3,334 በመጀመሪያ ዲግሪ ፕሮግራም የተመረቁ መሆናቸው ተገልጿል፡፡ዩኒቨርሲቲው ባለፉት 75 ዓመታት በትምህርት ልህቀት፣ በአመራር ልማት እንዲሁም በሀገር ግንባታ ያደረገው ዘላቂ እና ዘርፈ ብዙ አበርክቶ በምርቃት ስነ-ስርዓቱ ላይ ተዘክሯል፡፡ዩኒቨርሲቲው ከ75 ዓመታት በፊት ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ፤ የፈጠራ፣ ምርምር እና የዕውቀት መፍለቂያ በመሆን በርካታ መሪዎች፣ ባለሙያዎች እና ምሁራንን ማፍራቱ ይታወቃል።በሀገሪቱ የመጀመሪያው ራስገዝ ዩኒቨርሲቲ የሆነው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፤ ከ2017 ዓ.ም ጀምሮ በራሱ መመዘኛና መስፈርት ተማሪዎችን ተቀብሎ በማስተማር ላይ ይገኛል፡፡
#AddisAbabaUniversity#ClassOf2025#CommencementPhotos
EthioNews #Ethiopia