#AAU #JIGJIGA #KABRIDAHRአንጋፋው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቹን አስመረቀ።የአልማዝ ኢዮቤልዩ በዓሉን እያከበረ የሚገኘው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በዛሬው ዕለት ፦➡️ 3 ሺህ 334 የመጀመሪያ ዲግሪ፣ ➡️ 2 ሺህ 859 የሁለተኛ ዲግሪ፣ ➡️ 304 የሦስተኛ ዲግሪ እና 352 የስፔሻሊቲ እና ሰብ-ስፔሻሊቲ በአጠቃላይ 6 ሺህ 849 ተማሪዎችን አስመርቋል።በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ ተገኝተው ነበር።በሌላ በኩል በዛሬው እለት የጅግጅጋ እና ቀብሪድሃር ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎቻቸውን አስመርቀዋል።ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ከ1,500 በላይ ተማሪዎችን ያስመረቀ ሲሆን ከጎረቤት ሀገር ሶማሊያ የመጡ 13 ተማሪዎች ይገኙበታል።ቀብሪደሃር ዩኒቨርሲቲ ደግሞ ከ1,100 በላይ ተማሪዎችን አስመርቋል።

እንኳን ደስ አላችሁ ! ፎቶ፦ AAU (FMC)

EthioNews #Ethiopia