
በአጠቃላይ 7.5 ቢሊየን ችግኞችን ለመትከል ዕቅድ ተይዟል።በዛሬው ዕለት በወንዝ ዳርቻ ልማት አንዱ ክፍል በሆነው በእንጦጦ ዙሪያ ጠ/ሚ ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) ፣ የናይጄሪያ ምክትል ፕረዚዳንት ካቲም ሼቲማን ጨምሮ የክልል አመራሮችና ሚኒስትሮች በተገኙበት የችግኝ ተከላ ተካሂዷል።በዚህ ወቅት መልዕክት ያስተላለፉት ጠ/ሚ ዐብይ አሕመድ (ዶ/ር) ፥ የሚስማማውን ችግኝ በሚስማማው ቦታ እንዲተከል ጥሪ አቅርበዋል። የአረንጓዴ አሻራ በቀጣይ አመት ይጠናቀቃል የተባለ ሲሆን ኢትዮጵያ በአጠቃላይ በስምንት ዙር የችግኝ ተከላ መርኃግብር (የአረንጓዴ አሻራ ሲጠናቀቀ) የተከለቻቸውና የምትተክላቸው ችግኞች አጠቃላይ ብዛት 50 ቢሊዮን እንደሚደርሱ ይጠበቃል።
EthioNews #Ethiopia