ተወዳጁ ጋዜጠኛ ደረጀ ኃይሌ የጃምቦ ሪል እስቴት ብራንድ አምባሳደር በመሆን ዛሬ ሰኔ 19/2017 ዓ.ም በሂልተን ሆቴል የፊርማ ስነ ስርዓት ተከናወኗል።

የጃምቦ ሪል ስቴት ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ደበበ ሰይፉ በፊርማ ስነስርአቱ ላይ ባደረጉት ንግግር ጋዜጠኛ ደረጀ ኃይሌን በአምባሳደርነት የመረጥነው በብዙ መስፈርቶች ነው ያሉ ሲሆን ጃምቦ ካለው ዓላማ እና እንቅስቃሴ ጋር ተመሳሳይ እና ትክክለኛ ዓላማ ያለው መሆኑን ጠቅሰው ጋዜጠኛ ደረጀም ትክክለኛ ምርጫችን ነው ብለዋል።

ጋዜጠኛ ደረጀ ባደረገው ንግግር “የምችለው ጋዜጠኝነትን ብቻ ነው። ጋዜጠኝነት አልከፈለኝም ብዬ አማርሬ ግን አላውቅም፣ ጃምቦ ሪል እስቴትን አመሰግናለሁ” ብሏል።

ጃምቦ ሪል ስቴት ግሩፕ በወንድማማቾቹ አቶ ደበበ ሰይፉ እና አቶ ወንድራድ ሰይፉ አማካኝነት ጃምቦ ኮንስትራክሽን በሚል ስያሜ የተቋቋመ ሲሆን በሪል ስቴት ልማት ዘርፍ ከተሰማራ በኋላ ከ100 በላይ ፕሮጀክቶች ላይ የተሳተፈና በመሳተፍ ላይ የሚገኝ ግሩፕ መሆኑንም የጃምቦ ሪል ስቴት ግሩፕ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ኤፍሬም ጌታቸው ገልጸዋል።

ጋዜጠኛ ደረጀ ኃይሌ ጃምቦ ሪል ስቴት ግሩፕ ካስገነባው የሪል ስቴት ግንባታ በአፍሪካ ህብረት ከሚገኘው ሳይት ባለ ሶስት መኝታ ቤት የተሰጠው ሲሆን በብራንድ አምባሳደርነት አብሮ ለመስራት የሶስት አመታት ውል ፈጽመዋል።

ጋዜጠኛ ደረጀ ኃይሌ በቅርቡ በሰሜን አሜሪካን የኢትዮጵያውያን የስፖርት ፌስቲቫል ላይ ጃምቦ ሪል ስቴት ግሩፕን ወክሎ የመጀመሪያውን የስራ እንቅስቃሴ ይጀምራል።

EthioNews #Ethiopia