4 ሚሊዮን ብር ሐረር ገባ የሐረር ከተማ ነዋሪ የሆኑት አቶ መሐመድ ኢብሮ በ35ኛው ዙር የአድማስ ዲጂታል ሎተሪ በ1ኛው ዕጣ የ4 ሚሊየን ብር ዕድለኛ ሆነዋል ፡፡ አቶ መሐመድ በከብት እርባታ ላይ የተሰማሩ ሲሆን ከስራቸውም ጎን ለጎን ሎተሪን አዘውትረው የመቁረጥ ልማድ አላቸው ፡፡ በደረሳቸውም ገንዘብ እርባታውን እንደሚያስፋፉበት ገልጸዋል።