
ኢትዮጵያ መድን በታሪኩ የመጀመሪያ ዋንጫውን አንስቷል።
በሱፐር ስፖርት ያለፉትን አመታት በአዲስ ቅርፅ የቀጥታ ሽፋን ያገኘው ሊጉ የአምስት አመት የቀጥታ ስርጭት ውል በይፋ ተጠናቋል።
ሱፐር ስፖርት ባለፉት አመታት 802 ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ለተመልካቾቹ አድርሷል።
በቀጣይ አመት ሊጉ በአዲስ ቅርፅ ሊደርግ እንደሚችል የአክስዮን ማህበሩ ዋና ስራ አስኪጅ አቶ ክፍሌ ሰይፈ ፍንጭ ሰጥተዋል።
” አሁን እየተጫወትን ከምንገኝባቸው ሜዳዎች የሜዳ መጫወቻ ‘ Home ‘ አድርገው የፈለጉትን ከተማ እንዲመርጡ አስበናል ” ሲሉ ተናግረዋል።
” ውድድሩን አርብ ፣ ቅዳሜ እና እሁድ በየሳምንቱ ለማድረግ አስበናል ” ሲሉ ገልጸዋል።
ካለፉት ዓመታት ወዲህ ውድድሩ በተመረጡ ከተሞች ባሉ ስታዲየሞች ሲደረግ የቆየ ሲሆን ክለቦች መላ የቡድን አባላቶቻቸው ይዘው አንድ ከተማ ላይ ለሳምንታት በመቆየት ነው ውድድሩን የሚያደርጉት።
የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ የአመቱ ምርጥ እነማን ናቸው ?
➡️ የአመቱ ምርጥ ተጨዋች :- ሀይደር ሸረፋ ( ኢትዮጵያ መድን )
➡️ የአመቱ ምርጥ አሰልጣኝ :- ገብረመድህን ኃይሌ ( ኢትዮጵያ መድን )
➡️ የአመቱ ምርጥ ግብ ጠባቂ :- አቡበከር ኑራ ( ኢትዮጵያ መድን )
➡️ ወጣት ተጫዋች :- ይታገሱ ታሪኩ ( ኢትዮጵያ ቡና )
⏩ የአመቱ ምስጉን ዋና ዳኛ :- ማኑኤ ወልደፃዲቅ
➡️ የአመቱ ምስጉን ረዳት ዳኛ :- ሙስጠፋ መኪ በመሆን ተመርጠዋል።
EthioNewsSport #Ethiopia