
አርጀንቲናዊው ተጨዋች ሊዮኔል ሜሲ በእግርኳስ ህይወቱ ለመጀመሪያ ጊዜ የቀድሞ ክለቡን በተቃራኒው ሆኖ የሚገጥም ይሆናል።
በእግርኳስ ህይወቱ ለሶስት ክለቦች የተጫወተው ሊዮኔል ሜሲ በፒኤስጂ በነበረው ቆይታ ባርሴሎናን በተቃራኒው አልገጠመም።
ፔኤስጂ ታሪክ በማይዘነጋው የሻምፒየንስ ሊግ ምሽት በባርሴሎና ውጤት ሲቀለበስበት የነበረውን የተወሰነ ስብስብ ዛሬ በተቃራኒው ይገጥማል።
ሊዮኔል ሜሲ ፣ ሉዊስ ሱዋሬዝ ፣ ሰርጂዮ ቡስኬት ፣ አሰልጣኙ ዣቪየር ማሼራኖ እና ጆርዲ አልባ በውጤት ቀልባሹ የባርሴሎና ስብስብ ነበሩ።