ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና ምክትል ሊቀመንበርና የውጭ ጉዳይ ኃላፊ ሆነዋል።የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ (መድረክ) ” ታሪካዊ ” ሲል የጠራውን ጠቅላላ ጉባዔውን አካሂዶ አዲስ አመራር መምረጡን ይፋ አደረገ።” በሀገሪቱ ብቸኛው ቀዳሚ የብሔር ብሔረሰቦች የፖለቲካ ጥምረት ” እንደሆነ የገለጸው መድረክ 17ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔውን በተሳካ ሁኔታ በማካሄድ የውስጥ መነቃቃቱን የሚያበስር ወሳኝ እርምጃ እንደወሰደ ገልጿል።በግንባሩ ጽ/ቤት የተካሄደው ጉባዔ፣ አዲስ አመራር በመምረጥና እውነተኛ ዴሞክራሲያዊትና ሰላማዊ #ኢትዮጵያን 🇪🇹 ለመገንባት የሚያስችል ስትራቴጂካዊ አቅጣጫ በማስቀመጥ መጠናቀቁን አሳውቋል።አዲስ የተመረጠው አመራር፣ ወጣት አመራሮችን ከተመክሮና ልምድ ካካበቱ አንጋፋ ፖለቲከኞች ጋር በስትራቴጂካዊ ቅንጅት ያካተተ እንደሆነና ይህም መድረክ የኢትዮጵያን ውስብስብ ፖለቲካዊ ተግዳሮቶች በብቃት እንዲወጣ እንደሚያስችለው አመልክቷል።አዲሱ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ሆነው እነማን ተመረጡ ?1. አቶ ዓምዶም ገብረስላሴ ፦ የመድረክ ሊቀመንበር2. አቶ ሱልጣን ቃሲም፦ ምክትል ሊቀመንበርና የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ3. ወ/ሮ መርየም ሓሰን ፦ ምክትል ሊቀመንበርና የፋይናንስ ጉዳይ ኃላፊ4. አቶ ሙላቱ ገመቹ፦ ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበርና የህዝብ ድርጅት ጉዳይ ኃላፊ5. ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና ፦ ምክትል ሊቀመንበርና የውጭ ጉዳይ ኃላፊ6. አቶ ለገሰ ለንቃሞ፦ የመድረክ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ7. አቶ ደስታ ዲንቃ፦ የመድረክ ምክትል ጽህፈት ቤት ኃላፊ ሆነው ተመርጠዋል።መድረክ ፦- ዓረና ትግራይ ለዲሞክራሲና ሉዓላዊነት (ዓረና)፣ – የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ)፣ – የሲዳማ አርነት ንቅናቄ (ሲአን) እና የዓፋር ህዝብ ፍትህና ዲሞክራሲ ፓርቲን በአባልነት አቅፏል።ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃው የደረሰው ከመድረክ ህዝብ ግንኙነት ክፍል ነው።(NB. ከላይ የተያያዘው የመድረክ መግለጫ ነው)