
ኢትዮጵያ የባንክ ዘርፉን ለውጪ ባንኮች ክፍት ማድረጓን በይፋ አስታወቀች።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባወጣው መግለጫ የኢትዮጵያን የፋይናንስ ዘርፉን ለውጭ ባንኮች ለመክፈት የሚያስችለውን መመሪያ አጽድቋል።
ባንኩ፥ መመሪያ ቁጥር SBB/94/2025 ወይም “የባንክ ሥራ ፈቃድ፤ የእድሳት መስፈርቶች እና የውክልና ቢሮ መመሪያ ” መጽደቁን ነው ያስታወቀው።
በዚህ መመሪያ መሰረትም ለመጀመሪያ ጊዜ የውጭ ባንኮችን ጨምሮ ሌሎች ስትራቴጂክ ባለሀብቶች በኢትዮጵያ የባንክ ሥርዓት ውስጥ እንዲሳተፉ ይፈቅዳል።
ብሔራዊ ባንክ ትላንት ባወጣው መግለጫ ፥ ” የኢትዮጵያ የባንክ መስክ ለውጭ ኢንቨስተሮች ተከፍቷል፤ የውጭ ባንኮች እና ኢንቨስተሮች ማመልከቻቸውን ለብሔራዊ ባንክ ማቅረብ ይችላሉ ” ሲል አስታውቋል።
EthioNews ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
tru nw